(By T K, 13 december 2020) –
ኣናሳ…. ኮሳሳ…. ኣቨሳ.!
አሉህ በቁጥር ኣናሳ
መብት የለህ ባደባባይ ምታነሳ::
በስጋ ነብስም ኮሳሳ:
እያወቁህ በግብርህ ነብር: ኣንበሳ::
ረገጡህ እንደኣሽዋ
ዳግም እንዳትነሳ
ጠፍትህ እንድትረሳ::
ወይ ኣበሳ
ኣንተ የድር ኣንበሳ
መቼ ነው ምታገሳ!
ረጭቡህ በሽታ
ቀጥሎም የጥይት እሩምታ:
ገደሉህ በተርታ
እየጨፈሩ በደስታ
እየጨሁ እልልታ::
ይህ እንዳያበቃ
ጭሆትህ ተነጥቃ
ወነጀሉት መኸተ
ላንተ ለቆመው ጥበቃ::
ወይ ኣበሳ
ኣንተ የድር ኣንበሳ
መቼ ነው ምታገሳ!
ዘግተው በሩ በስንስለት:
እንደ ቤተ ትምህርት,
እድገት በል ጤንነት ትካላት
በጨለማ እንድትኖር ግዞት
እስከ ምፃዓተ እለት::
ወይ ኣበሳ
ኣንተ የድር ኣንበሳ
መቼ ነው ምታገሳ!
በሁለት እግር ሚራመዱ
ግን በሌላ ባለ ሁለት እግር የሚናደዱ
በስላም ካደረ
ከጠገበ ሆዱ
ራስ ቀና ካለ
ማየት ካሰተዋለ
መራመድ ከቻለ
ንሮ ካሽነፈ ከተስተካከለ::
ሌላ ስው ከረዳ
ከወደቀው ጏዳ
በምስቅልቅል እዳ:
እይናቸው ደም ስርፆ
በቅናት ሚፈነዳ:
ሆዳቼው በተቅማጥ ናዳ::
ይቅር ከዚህ ዘር
መጋባት ይሁን እብሮ መኖር::