ትግራዋይ እውነት ነው!

Poems

(ብሰላም ትግራወይቲ, 24  ለካቲት 2013 ዓ/ም) –

ትግራዋይ እውነት ነው!

ሰበዙ ሲመዘዝ:
ክፍተቱ ሲሰፋ፣

ውጥንቅጡ ወጥቶ:
ቅጥ አምባሩ ጠፍቶ:
መያዣውን አጥቶ:
ማጣፊያውም አጥሮ፣

አንዱም ላይጠገን:
ሸርሸሮ ገዝግዞ:
ህሊናን አድምቶ:
ህልውናን ረግጦ:
በነፍስም በስጋ:
ፈልጎና አሳዶ:
መድረሻ አሳጥቶ:
ሊበላህ የመጣ:
የአውሬዎች መንጋ፣

በደቦ ዶልቶ:
በምስራቅ በምዕራብ፡
በሰሜን በደቡብ፡
ዙሪያ ምላሽ ዘግቶ፣

ሊያደርግህ እንኩቶ:
አልሞ ጎምዥቶ፣

በሶስት ቀናት ፕላን:
ዳንኪራ ወጥኖ:
ተንኮል አጠንጥኖ:
ሴራና ደባውን ደምሮ ቀምሮ:
አንዱም አልተሳካ አልረባም አልቀና።

እንዳሰቡት ሳይሆን
አሰቀድሞ ነቅቶ
የሸፍጥ ሚዛኑን አዛብቶና አናግቶ
ሃቅና መርህን ዘወትር አንግቦ
ትግራይ ይፋለማል
ዛሬም ነገም ድሮ።

ወደድንም ጠላንም
ይሄ ህዝብ ልዮ ነው
ታሪክ ነው፣ ቅርስ ነው
ቃል ነው፣ ሃይማኖት ነው
ሃቅ ነው፣ ፍትህ ነው
ይህ የጎደለ ቀን፣
ወያናይ ትግል ነው
ትግራወይቲ እምነት
ትግራዋይ እውነት ነው።

ትግራይ ትዕወት

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *