የቀን ጅቡ ማነው?

Poems

(በኢየሩሳሌም, 02 March 2021) –

የቀን ጅቡ ማነው፧

ገና አግሩ ሳይገባ
በሶስተኛው ወር ላይ
ሽህዎችን ሰብስቦ
መስቀል ኣደባባይ
መነጽር ድቅኖ
ውሸታሙ ኣይኑ ላይ
ታስታውሳላችሁ፧

ኣማርኛ ቋንቋ
የማይገባን መስሎት
የቀን ጅቦች ብሎ
ሲጣራ ያለፍረት
ብጅምላ ሲሳደብ
ሲጨበጨበልት

ታድያ ጅቡ ማነው
በገዛ ህዝቡ ላይ
ወራሪ ሰስቦ
ሽዎች የገደለው
የጂብ መንጋ ጠርቶ
አጥር ኣስፈርሶ
ተጋሩን ያስበላው
ማነው፧ እኮ ማነው

የቀን ጅቡ ማነው፧

ጀነራል ሰኣረን
ጀነራል ገዛኢን
በሞቀ በታቸው
በጠራራ ጸሃይ
ልኮ ያስረሸነው
እኮ ጅቡ ማነው?

እናት ታለቅሳለች
ልጆች ይሞታሉ
ብሎ የዛተብን
ያን ርኩስ እቅዱን
በተግባር ሊያሳየን
በጭለማ ገብቶ
ተኩስ የለቀቀብን

ማነው፧ እኮ

የቀን ጅቡ ማነው፧
መቸ የቀን ብቻ
የጭለማውም ጅብ
ንጹህ ደም የሚያፈስ
ለሰልጣን ስግብግብ
ለሰው ክብር የለው
ላገር ልኡልነት
ትግራይን ጨፍጭፎ
የሚሰብክ ኣንድነት
ለዛ ሁሉ ሽፋን ህግ ኣስከባሪነት

እኮ
ማነው ጅቡ የቀን የጭለማ
ተጋሩን በጅምላ የወጋ ያደማ
በያሉበት መንደር
ጅቦችን ሰብስቦ
በካራ በጥይት
በቦምብ ኣስደብድቦ
ያስግደለው ማነው?

የኢሳያስ ጥጃ
ያማሮች ከበሮ
መደመር የሚሰብክ
የማይችል ደምሮ
ከመንገስ ባሻገር
የማያይ ኣዙሮ
ስብእናን የማያውቅ
የሌለው ኣእምሮ
ኣለም የሚመስለው
እንደሱ ደንቆሮ
ማነው?

የበግ ለምድ ለብሶ የዋህ የመሰለ
በሰበካ ቃላት ስንቱን ያታለለ
የድያቢሎስ ፈረስ የጅቦች ኣለቃ
ግፉ ቢዘረዘር ቃላት የማይበቃ

ታድያ ጅቡ ማነው?

የተጋሩን ስጋ
በጠራራ ጸሃይ
የቀን ጅብ ያስበላው
ወንጀሉን ኣለም ሲይቅ
ሸምጥጦ የሚክደው
ማነው?

ትግራይን ያደባየ ተጋሩን የቀጠፈ

ማነው?
ማይ ካድራ ሳምረ ላይ
ሓውዜን ና ኣድዋ
እንዲሁም ሑመራ
ረሽኖ ያረገፈ
ቅድስቲቱ ኣክሱም ላይ
ስመንት መቶ ሰዎችን
ጽላተ ሙሴን ሊዘርፍ
አንደ ቅጠል የረፈረፈ
ህ.ግ.ደ.ፍ ጋር ኣብሮ ንብረት የዘረፈ

የህጻን የወጣት
የሴት መነኮሳት
ክብርን የደፈረ
የገደለ ካህናት
ስንቱ የዘረዘራል
የቀን ጅብ የሚል ስም
ለሱ መች የበቃል

እንደ ከብት ኣጋድሞ
ክቡር ደማቸውን
የደፋ ያስደፋ
የራሱን ስም ሮጦ
ከሰው ላይ ልጠፋ

ማነው
ማነው ታድያ ጅቡ
ኣገር የሚያምሰው
በጉራ በስድቡ?

ሽረና መቐለ
ከራያ እስከ ሳምረ
ውቅሮና ኣዲግራት
ደብረዳሞ ኣልቀረ
ነጋሽ ታሪካችን
የኣፍሪካ ሜካችን
ቦምብ ያዘነበበት
ከብትና ህዝባችን

ማነው ታድያ ጅቡ
ኣገር የሚያምሰው
በጉራ በሲድቡ?

ማርያም ጉንዳጉንዲ
ከለዓሳ ዓሊተና ዓሲምባ
ስንቱ ይዘረዘራል
ድፍን ዓዲ ኢሮብ
ሲያልቅስ ደም ሲያነባ
በግፍ ያሰቃየ
የሚገድል የሚያስርብ
ሌላ ስም የልውም
ካልሆነ የቀን ጅብ

እነ ስዩም መስፍን
እነኣባይ ጸሃየ
የጲላጦስ ወንድም
በደም የጨቀየ
ኣይነ ስውር ገድሎ
ሲያመልጥ ያዝኩት የሚል
እጅና ኣይኖቹን
ያጣውን በትግል
ኣልነበረም እንዴ
ያንን ጀግና ኣስመላሽ
ድብን ኣርጎ ሲገድል
ታጋይዋን ኣልጋነሽ
የማይሰቀጥጠው
ሽምጥጥ ኣርጎ ሲዋሽ
እነ ሴኩቱሬ
እንዲሁም ዘረኣይ
በቀን የረሸነ
ኧረ እሱ ኣይደለ ወይ
ቆጥሮ ለመጨረስ
ኣመት ያስፈልጋል
ኣሰቃቂ ግፉ
በታሪክ ይጻፋል

ጅቡ ማነው ታድያ
የማታና የቀን
ተጋሩን በነቂስ
ለእልቂት የዘፈቀን
ዝም ኣትበሉ እንጂ
የቀን ጅቡ ማነው?
ኣገሩን ከጫፍጫፍ
እሳት ያነደደው?

ገና አግሩ ሳይገባ
በሶስተኛው ወር ላይ
ሽህዎችን ሰብስቦ
መስቀል ኣደባባይ
መነጽር ድቅኖ
ውሸታሙ ኣይኑ ላይ

ታስታውሳላችሁ?

ኣማርኛ ቋንቋ
የማይገባን መስሎት
የቀን ጅቦች ብሎ
ሲጣራ ያለፍረት
ብጅምላ ሲሳደብ
ሲጨበጨበልት

ታድያ ጅቡ ማነው?
በገዛ ህዝቡ ላይ
ወራሪ ሰብስቦ
ሽዎች የገደለው
የጂብ መንጋ ጠርቶ
አጥር ኣስፈርሶ
ተጋሩን ያስበላው
ማነው፧ እኮ ማነው
የቀን ጅቡ ማነው፧
ፍርዱን ለታዛቢ
ለፍትህ እንተወው።

 

1 thought on “የቀን ጅቡ ማነው?

 1. Excellent Poem. Keep up the good work.

  The hyena who requested a hide in a place where its bad behavior is not revealed is the perfect example of Abiy and his fans, Amhara chauvinists. Amhara elites people are children of satan as thier deed speaks louder than thier pretencious words.

  There was a man in amhara region . I prefered to omit his name for his personal security and saftey. One day he told to his son. The father said, Look at my granary (tradtional grain store hut), I have threshed my harvest (grains) on the sky.

  The father continued to brag saying, your father, I am an indefatigable and assiduous man in the village.

  The kid was ery happy with the story told by his father . And He felt fantasied and uttered father please help , ‘the sraw poked my eyes?? The father was very anxious and saw his son and he cannot find anything in his eyes . The father started to laugh as the lies of his son made him to immerse in an infectious belly laugh. He said to his son’ your lies surpassed mine.

  Hence, Amhara elites are more atrocious and brutal liars than the devil himself . When I was a kid there were youngesters who carry a tiny movable and poratble box made of carton to sell cigarate,stationery(pen, pencil, sharpener) chewing gum. This box is locally called ሱቅ በደረቴ፥. I find amhara elites and Abiy to have engaged in business being a sophticated and ordinary liars(ሱቅ በደረቴ፥ ዉሸት በደረቴ(ሀሰት በኪሴ ብላችሁ ብትጠሩ ትችላላቹህ)፥፥እኔ ግን አቢይ ዉሸት በደረቱ ብለዉ እመርጣለሁ፥ምክንያቱም ከኪሳችን ደረታችን በጣም የቀረበ ነዉ የአማራ ልሂቃንም ሆኑ ኮረኔል አቢይ ፥ጀሌዎቹ የዩቱብ የሀሰት ጅምላ ነጋዴዎቹ አይኔን ግንባር ያድርገዉ ብለው ሲዋሹ ጥቂት እኳን አይዳዳቸዉም፥ማለቴ ሲዋሹ ያለምንም ችግር በፍጥነት ይዘረግፉታል፥የራሳቸዉን ወገን በየደቂቃዋ ዉሸት እየፈበረኩ አንዴ ወያኔ ተደረመሰ፥ወያኔ ገንዘብ ሲያከማችበት የነበረዉ የምድር ዉስጥ ባንክተገኘ፥ሌላ ጊዜ በወያኔ ኪስ ዉሥጥ ጉድ ተገኘ እያሉ ልጆቹንና ገንዘቡን የሰጣቸዉን ሕዝባቸዉን የሀሰት ስንቅ ያሸክሙታል፥

  ጉድ ተገኘ የሚለዉን ቃል አብዝተዉ ይጠቀሙታል እዉነታዉን ለማደባበስ ና በዝርዝር እንዳይ ገልፁት ሌላ ጥያቄ ስለ ሚጭር (ስለሚያስነሳ)ከጥያቄ ለመዳን ሰላምና ድል የተራበ ሕዝባቸዉን ጉድ ተገኘ እያሉ ጉድና ጉዳንጉድን ይቀልቡታል መጥኔ ይስጣቸዉ፥

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *