በጥላሽ ለቆሙት!

Poems

(ብተመስገን ከበደ: 27 ለካቲት 2013 ዓ/ም, 06 March 2021) –

በጥላሽ ለቆሙት!

ይቅርብኝ ኣልጠጣም
ጉሮረዬ ይድረቅ
የእባብ ምሽግ መስሎ
እርሻውም ይስንጠቅ

እህህ ልበል እንጅ
ዴኛ በሌለበት ፈራጅ
ህግ ባልቆመበት ሃግር
ውንጀል እንደክብር
ወሮ በላ እንዳሻው የሚሽክረከር
ሥራ ቢሉ ስትኛ ኣዳሪ
ትምህርት ቢሉ ደብተራ ኣዝማሪ::

ይህ እንዳልበቃ ዳግመኛ
ምን ያክል ጉደኛ
መከራየን ችዬ ኣርፌ እንዳልተኛ
እየተዝመገመገ: እዬተሙለገለገ
ባዕድ ሃገር ኮብልሎ
መጣ ጠላት ኣከትሎ
ምንም ብያጎርሱት
ምንም ቢያጠጡት
ሆዱ እስኪጥለቀለቅ
ይብቃኝ የማያውቅ
ኣውሬ ይዞ መጣ
ጥርሱ ከነከስ ፈፁሞ የማይለቅ
ወይ ኣቺ ማርያም ፃዲቅ
ምን ሃጥያት ቢፈፀም ነው
ይህ ሁላ እልቂት
በጥላሽ ለቆሙት::

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *