ይገባሻል ክብር

Poems

(በሰላም ግደይ: 9 መጋቢት 2013) –

ይገባሻል ክብር

በስቃይ ውስጥ ፅናት
በሀዘን ፈገግታ፣
እንቅልፍ በሌለበት
የህልሞችሽ ተስፋ፣
በጭለማ ብርሃን
በጠማማው ቀና፣
በደረቀው ለምለም
በገደሉ ሜዳ፣
በመሞት መኖርን
ወድቆ መነሳትን፣
በምድር ያልታየ
ፍፁም ያልተሰማ፣
የአረመኔዎች ግፍ
የአውሬዎች ክፋት
ኢ-ሰብአዊ ፍርድ
ከቶ የማይሰብራት፣
የህሊና ፍትህ
ከቶ የማይነጥፍባት፣
በእውነት ማሸነፍን
በመርህ መሞትን፣
በትግል ነፃነትን
ሰንቃ በደሟ
የአያት የቅድመ አያት
ታሪኳን አቅባ፣
ይህቺ ትግራወይቲ
ያቺ የትግራይ እናት
እህት ወጣት
ልጅ ሴት፣
ይገባታል ክብር
ፍፁም ልዕልና።

አይዞሽ ከፍ በይልን
ቅኗ የኛ ብርቱ፣
ብዙ ሩቅ አይሆንም
ደመናው መጥራቱ
በፀሐይ መፍካቱ፣
ሰማይና ምድርን
አድማስን ያቀና፣
ፈጣሪ አይረሳሽም
አንቺ የሱ ነሽና፣
አሁንም ዘወትር
ይገባሻል ክብር
ፍፁም ልዕልና።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *