ተመስገን ምን ከበደ!

Poems

(በተመስገን ከበደ: ሰኔ 03, 2013) – 

ተመስገን ልበል ምን ይከብዳል
ተመስገን ከማለት
ባይሞቀኝ በዱለት
ባልስቅም ባልንከተከት
ባልቀምስም ጮማ ወይ ዱለት
ተመስገን ባለማለት
ኣለማወቅ ነው
የባሰ ችግር ዳገት
አለ በሰው ተፈጥሮ
ራሱን ሽቅብ  ሰቅሎ
አሎህ አሎህ
ኣወቅኩኝ ሲል
ማን ከኔ ሌላ
ባለ ብዙ መላ
ሌሎችን ሲያስጥላላ
ሄዶ ሄዶ በመጨረሻ
ዘጭ ይላል እንዳተላ
ኣተላነቱ እንደተጠበቅ ሳይላላ
ያምባገነን ድንፋታ ሜላ
ከፊት ሆነ ከኅላ

እየቀጠቀጡ በዱላ
እግር ኣስሮ በስንስለት
እጅ ስብሮ በጥምብ ብረት
ሆድ ኣርዶ በስለት
ጅርባን ኣርሶ በግለት
ኣንበጣ ውርጭት ሚደሰት
ግን በሰው ጀርባ መርዝ ሚረጭ
ህፃና ደፍሮ ማህፀን የሚቆጭ
ጭካኔው ኣንድም የለው ሁለት
ዘመድ ኣይቀር ጎረቤት
ሁሉንም የሚለክፈው የሱ ኣንደበት
ከዚያም ከዚህ ወድያ
ማን ቀረ ለክፋቱ ማርክያ
የሞተ ሙቶ
የሽሽም ሸሺቶ
ፈሪ አንገቱን ደፍቶ

ሀገር ባዶ ቀርቶ
ደጅ በርዋ ተከፍቶ
ለጠላት ተመችቶ
ዕድሜ ለሱ ሰው በላ ዲሪቶ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *